ጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪ አልባ ሆኗል

Views: 73

በጅማ ዩንቨርስቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ወደ መጡበት እንደተመለሱ እና ዩንቨርስቲው ውስጥ ምንም ተማሪ እንደሌለ ምንጮች ለኢትዮ ኦንላይን ገለጹ፡፡ በአንፃሩ፣ ጅማ ከተማ  በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ለማወቅ ተችሏል፤ በከተማው የሚፈጠሩ ኹከትና ግጭት የሚጀምሩት ከሌላ አካባቢ የመጡ ራሳቸውን ‹‹ቄሮ››ብለው የሚጠሩ ቡድኖች ናቸው ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጸዋል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ያልሆኑ ወጣቶች በመግባት፣ አማራ ከዩንቨርሲቲያችን ይውጣልን በማለት ግጭት እንደቀሰቀሱና ተማሪዎችም በነበረው አለመረጋጋት በመረበሽ ወደ ሀይማኖት ተቋማት እና ወደ ስታዲም ሄደው እንዲጠለሉ የግቢው ማህበረሰብ እንደተባበራቸው ተማሪዎች አሳውቀዋል፡፡

በሀይማኖት ተቋማቱ እና በስታዲየም የተጠለሉት ተማሪዎች፣ አብዛኛዎቹ ወደ መጡበት አካባቢ የተመለሱ ሲሆን፣ አንድ-አንድ ተማሪዎች ደግሞ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች ተደብቀው እንዳሉ በዩንቨርስቲው የአንደኛ ዓመት ተማሪ የሆነችው የኢትዮ-ኦንላይን የዜና ምንጭ ተናግራለች፡፡

በሌላ በኩል፣ ጅማ ከተማ በተለመደው ዓይነት መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ ለማወቅ ተችሏል፤ ነገር ግን በከተማዋ አንድ አንዴ የሚስተዋሉ ግርግሮች የሚፈጠሩት ከአንድ አንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ወደ ጅማ ከተማ በገቡ አዳዲስ ነዋሪዎች (ራሳቸውን ቄሮ) ብለው በሰየሙ ወጣቶች የሚከሰት አለመረጋጋት እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

“ጅማ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ከተማ ናት እንጂ አንዱን ብሔር ለይታ ውጣልኝ  የምትል ከተማ አይደለችም” ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

‹‹ይህ ሰዎችን በብሔር ነጥሎ የማግለል ድርጊት፣ የጅማ ከተማ ነዋሪን በፍጹም አይወክልም›› በማለት፣ ተግባሩን በማውገዝ አጥብቀው እንደሚቃወሙት ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com