ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ኢሳት ቴሌቪዥን የሀሰት ዘገባ አስተላልፏል ሲል ወነጀለ

Views: 103

ኢሳት ቴሌቪዥን ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም በዕለታዊ ዝግጅቱ  በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ግጭት ተቀስቅሶ 10 ተማሪዎች እንደቆሰሉ አርጎ መዘገቡ ፈፅሞ ከእውነት የራቀ መረጃ ነው አለ፡፡ በጉዳዩ ላይ በስልክ ምላሻቸውን የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቭዥን ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሳባ አታሮ ጊዜ ስጡኝና በኢሜል ምላሽ እሰጣለሁ ብለዋል፡፡

በቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ምንም ዓይነት ግጭትም ሆነ የተጎዳ ተማሪ የለም፤ ይህ ዘገባ እውነት አይደለም ሲል ዩንቨርስቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።

ዩኒቨርሲቲው በመልዕክቱ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በእንዲህ ዓይነቱ ሀሰተኛ መረጃ ሳይረበሹ እና ቦታ ሳይሰጡ እውነተኛውን መረጃ ከታማኝ ምንጮች በመስማት እራሳቸውን ማረጋጋት ይኖርባቸዋል ብሏል።

በአጠቃላይ ኅብረተሰቡ ትክክለኛ ባልሆነ ዘገባ ሳይሸበር ለሀገር ሰላም ዘብ መቆም ይኖርበታል ብሏል።

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ሥራ አስኪያጅ ምላሽ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com