ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የተፈናቀኑ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ባሕር ዳር አቀኑ

Views: 74

በጂማ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የአማራ ክልል ተወላጅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ በቡድን በተደራጁ ብሄርተኛ ኃይሎች መደብደባቸውንና ዛቻ እንደደረሰባቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በድብደባው ከዩኒቨርሲቲው የተፈናቀሉ 28 ተማሪዎች ትናንት ምሽት ደብረ ማርቆስ ከተማ የገቡ ሲሆን፣ ዛሬ ወደ ባሕር ዳር መጓዛቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የጂማ አካባቢ ተወላጅ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ተማሪዎቹ እንዳይፈናቀሉ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

ተማሪዎቹ በደብረ ማርቆስ በነበራቸው ቆይታ፣ በቦታው በሚገኘው የአማራ ወጣቶች ማሕበር አቀባበል እና መስተንግዶ ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡

ተማሪዎቹ ወደ ባሕር ዳር ያቀኑት፣ የክልሉ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

አሁንም ቢሆን፣ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ልዩ-ልዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በልዩ ልዩ ቤተ እምነቶች ተጠልለው እንደሚገኙ ለኢትዮ-ኦንላይን ዘጋቢ ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በዩኒቨርሲቲዎች በሠላማዊ የመማር ማስተማር እና የመልካም አስተዳድር ጉዳዮች ዙሪያ፣ በባሕር ዳር ከተማ ውይይ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

በውይይቱ የ47 ዩኒቨርሲቲዎች የለውጥና የመልካም አስተዳድር ዳይሬክተሮች፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com