በአሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ

Views: 140

በአሜሪካን የገንዘብ ሚንስትር ጋባዥነት ተሰናዳ በተባለው እና በውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመራው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረውን ውይይት አጠናቋል::

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ እና አምባሳደር ፍጹም አረጋ ጉዳዩን አስመልከተውም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::

በውይይቱ ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ ፍትሃዊና ሚዛናዊ የውሃ መብት እንዳላትም አስገንዝባለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ 70 ሚሊዮን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ያልቻለ ህዝቧን ተደራሽ ለማድረግ እና ለድህነት ቅነሳ ጥረቷ እንጂ፣ ማንንም አካል የመጉዳት ዓላማ እንደሌላት ማስረዳቷንም በመግለጫቸው  ላይ ተነናግረል፡፡

በግድቡ ዙሪያ ያሉ ማናቸውም አለመግባባቶች በቴክኒክ ባለሙያዎች ሙያዊ ምክክር ብቻ እንደሚፈቱም ኢትዮጵያ እደምታምን አስረድታለች ነው የተባለው፡፡

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የነበሩ ብዥታዎችን ግልጽ ለማድረግና የኢትዮጵያ አቋም ገንቢ መሆኑን ለማስረዳትም የምክክር መደረኩ ጠቃሚ እንደነበረም ተብራርቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ በቦታው በመገኘት ሪቫን አብረው በመቁረጥ ለመመረቅ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን ታናግረዋል ተብሏል፡፡

በተደረገው ውይይት መሠረትም የሦስቱ አገራት ሚኒስትሮች በታላቁ የህዳሴ ግድብ አሞላል ዙሪያ ገንቢ፣ ቀጣይነት ያለውና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስምምነት ላይ ለመድረስ መግባባታቸው ተገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com