የሲዳማ ክልል ሕዝበ ውሳኔ የመራጭነት ምዝገባ መካሔድ ጀምሯል

Views: 188

የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ዛሬ፣ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም በሁሉም የሲዳማ ዞኖች የተጀመረ ሲሆን፣ ለቀጣይ ዘጠኝ ቀናት እንደሚቆይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በርካታ ሰዎችም ምዝገባ እያከናወኑ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ቦርዱ ሕዝበ ውሳኔውን ለማከናወን ለወራት ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ለምርጫው ስኬትም ከስድስት ሺሕ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎችን አሰልጥኖ ማሰማራቱ ይታወሳል።

ምርጫ ቦርድ በሲዳማ ዞን አስተዳደር እና በሐዋሳ ከተማ መስተዳድር 598 ቀበሌዎች 1692 የምርጫ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን አስታውቆ ነበር።

(ዘገባው የአዲስ ማለዳ ነው)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com