በጉጂ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አጠፋ፤ በርካቶችን ለጉዳት ዳረገ

Views: 159

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጉጂ ዞን፣ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የመኪና አደጋ፤ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ በርካቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት በጉጂ ዞን ዋደራ ወረዳ በደረሰው የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በርካታ ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች፣ በአዶላ- ዋዩ አጠቃላይ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com