ማንነትን መሠረት አድርጎ የተፈፀመው ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ኢሃን ጠየቀ

Views: 187

ሰሞኑን በኦሮሚያ፣ በድሬ-ዳዋ እና በሀረር የተፈፀመው ማንነትን መሠረት ያደረገ ግድያ፣ በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን የኢትዮጵያውያን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሀን) ፓርቲ መንግሥትን ጠይቋል፡፡

ፓርቲው ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው በተጨባጭ የሆነው ሁሉ በገልልተኛ ወገን እንዲጣራ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ አሳውቋል፡፡

‹‹ጉዳዩን ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል አለባብሶ ማለፍ፣ በዜጎች ሕይወት እንደመቀለድ ይቆጠራል›› ብሏል- ኢሃን በመግለጫው፡፡

በሀገር ውስጥ የፀጥታ ችግሩ በዚህ ኹኔታ ከቀጠለ፣ መጭውን ምርጫ በሠላም ለማከናወን አስቸጋሪ እንደሚያደርገው አሳስቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ኗሪዎች፣ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበርም የኢትዮጵያውያን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com