በአማራ ክልል የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ለበጎ ፈቃደኞች ጥሪ ቀረበ

Views: 210

በአማራ ክልል የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል፣ ለበጎ ፈቃደኞች ጥሪ ቀረበ፡፡

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ እና በኦሮሞ ዞን በስምንት ወረዳዎች እና በ23 ቀበሌዎች የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ለኢትዮ-ኦንላይን አስታውቋል፡፡

የመካለከል ሥራው በአውሮፕላን እና በሰው ኃይል ኬሜካሎችን በመርጨት እንዲሁም የአንበጣ መንጋን ሊረብሹ እና ሊያባርሩ በሚችሉ እንደ ጥሩምባ፣ ፊሽካ እና ፓውዛ ወይም መብራት በመጠቀም የመከላከል ሥራው እየተሰራ ነው  ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን የተናገሩት የክልሉ የግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ አለባቸው አሊጋዝ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት የደረሰውን የግብረና ምርት በአንበጣ መንጋው ከመውደሙ በፊት አርሶ አደሩ ምርቱን እንዲሰበስብ አቶ አለባቸው አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም የአንበጣ መንጋው አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ በሰብል ላይ ጉዳት ሳይደርስ የመካለከሉ ሥራ በጋራ ለመሥራት ለክልሉ ነዋሪዎች እና ለበጎ ፈቃደኞች ጥሪ ቀርቧል፡፡

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል በጎንደር አስተባባሪ የሆነው ቶማስ ጄጃው  የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ቁጥራቸው ብዙ የሚባል በጎ ፈቃደኞች መኖራቸውን ለኢትዮ-ኦንላይን አስታውቋል፡፡

የባህርዳሩ አስተባባሪ ስንታየሁ ታከለ እንደገለጸው የአንበጣ መንጋው አሳሳቢ በመሆኑ፣ ሕብረተሰቡ አስቀድሞ መከላከል እንዳለበት፤ እንዲሁም ጊዜውን እና አቅሙን በበጎ-ፈቃድ በመስጠት  የሚችለውን ያህል በዘመቻው እንዲሳተፍ  ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ይህም የሚሆነው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆኑ እንደሆነም አስተባባሪዎች ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ዘመቻ ላይ እንዲሳተፉም ወጣቶች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ ተማሪዎችን እና ባለሃብቶችን በማስተባበር የመከላከል ሥራ በይበልጥ እንደሚሰራም ተነግሯል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com