ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር እንዳይገባ የቁጥጥር ሥራ ተጠናከረ

Views: 231

ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ፣ የቁጥጥር ሥራዎች መጠናከራቸው ተገለጸ፡፡

በኮንትሮባንድ የሚገባ የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ቤት እንዳይገባ የቁጥጥር ሥራዬን አጠናክሬያለሁ ያለው የገቢዎች ሚኒስቴር ነው፡፡

የተለያዩ የዓልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) የጦር መሣሪያ መለዋወጫዎች በ‹‹ዐረቢያን መጅሊስ›› መቀመጫ ፍራሽ ውስጥ ተደብቆ በሕገ-ወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ መያዙን አሳውቋል፡፡

የጦር መሣሪያ መለዋወጫዎች በ‹‹ኤክስሬይ›› እና በእቃ ፍተሻ መኮንንኖች መያዙም፣ የቁጥጥር ሥራው አንዱ አካል እንደሆነ ሚንስቴሩ ለኢትዮ-ኦንላይን ገለጿል፡፡

በአሁን ወቅት ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች በተለያዩ መንገዶች ዘዴዎቻቸውን እየቀያየሩ መምጣታቸውን የተናገሩት የሚንስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል፤ እኛም ይህን አውቀን የቁጥጥሩ ሥራ ላይ ጠንክረን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ኬላ ላይ የፍተሻ ሥራዎችን የሚሰሩ ባለሙያዎቻችን የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው፤ በቅርቡም አንድ ባልደረባችን በጅግጅጋ ሕይወቱ አልፏል- ሲሉ ወ/ሮ ኡሚ ነግረውናል፡፡

ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ታርጋ በመቀያየር፣ ዋና መንገድን ትቶ በጫካ ውስጥ እያቆራረጡ መሄድ እና የተለያዩ መንገዶችን እየዘየዱ ሲሆን፣ በትላንትናው ዕለትም፣ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ በኩል ሊገባ የነበረው የተለያዩ የዓልሞ ተኳሽ (ስናይፐር) የጦር መሣሪያ መለዋወጫዎችንና መሳሪያዎቹን ለማስገባት የሞከረው ተጠርጣሪ ግለሰብም በቁጥጥር ስር እንደዋለ ሚንስቴሩ አስታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com