ባሻ በልሁ አባ ቆሮ እና ጓደኞቹ ሲታወሱ

Views: 208

ሁለት ሜትር ከአስር ሳንቲ ሜትር ቁመት የነበረው ባሻ በልሁ አባ ቆሮ በክቡር ዘበኛ የማርሽ ባንድ ውስጥ ታምቡር መች ወጣት ነበር።

ባሻ በልሁ አባ ቆሮ በጣልያን ወረራ ወቅት በጣልያን አልገዛም ብሎና ብሔራዊ ዐርበኞችን ደግፎ ስለነበር፣ የፋሽስት ጣልያን ወታደሮች አሳደው ይዘው አሰሩት፡፡

ለፋሽስት አልገዛም ብሎ በእምቢተኝነቱ ስለገፋበት አሰቃይተው ገደሉት። ከእርሱም ጋር አብረው ከተገደሉት መካከል የክቡር ዘበኛ የማርሽ ባንድ አባል የነበሩት ጓደኞቹ፡- ሾጎ ቆቲ፣ ታምሩ ተሰማ፣ ጳውሎስ ገዲማ እና ሳሙኤል ይማም ይገኙበታል።

ስዕል ፩፡- ባሻ በልሁ የክብር ዘበኛን የማርሽ ባንድን ሲመራ፤ ቦታው ፒያሳ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ በታች፤ጊዜው ፩፱፲፳፮ ዓም።

 

ስዕል ፪፡- ባሻ በልሁ በአሰልጣኙ የስዊስ ሰው እና በክቡር ዘበኛ አለቃ ሲጎበኝ፤ ቦታው የቀድሞው ገነተ ልዑል ቤተመንግሥት፤ ወይም የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመኮንን አዳራሽ መግቢያ ዋና በር ፊት-ለፊት።

ለተጨማሪ መረጃ፡- የትምክሕት ተፈራ-ን፣ ስለ-ኢትዮጵያ ሙዚቃ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈውን (Ethiopian Popular Music History) ጽሑፍ ያንብቡ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com