የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረውን የርሃብ አድማ ወደ ደም ልገሳ ቀየሩት

Views: 174

ሰባ አንድ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ-መሪዎች፣ አዲሱን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓዋጅ በመቃወም ሊያካሂዱት ያቀዱትን የሁለት ቀናት የርሃብ አድማ ፕሮግራምን ሰረዙ፡፡

የርሃብ አድማው በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ሊከናወን ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ያልተከናወነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር እውቅና ሰጥቶ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኑ መሆኑን ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል፡፡

ከተማ አስተዳድሩ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አለመስጠቱን የገለጹት ፓርቲዎቹ፣ ከተማ አስተዳድሩ ተባባሪ በሆነ ጊዜ በዓዋጁ ላይ ያላቸውን ተቋውሞ፣ በርሃብ አድማ እንደሚገልፁ ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የርሃብ አርድማውን ለማድረግ የወጡ የፓርቲ- መሪዎች ግን በብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት በመገኘት ደም ይለግሳሉ፤ መሪዎቹ የሚለግሱት ደም በሰሞኑ ግጭት ለተጎዱ ዜጎች ጥቅም እንዲውልም ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ አዲሱን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓዋጅ ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ ያላገናዘበ እና የፓርቲዎቹን አንጋፋነት የሚክድ እንደሆነ በመግለፅ ነው የተቃወሙት፡፡

ፓርቲዎቹ ከተቃወሟቸው አንቀፆች መካከል፣ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች በፓርቲነት ለመመዝገብ ቢያንስ አስር ሺህ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ እንዳለባቸው የሚገልፀው አንቀፅ አንዱ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com