በጄኔራል ሠዓረ ግድያ የተጠረጠረው ፲ አለቃ መሳፍንት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ

Views: 192

ከሰኔ 15ቱ የጄኔራል ሠዓረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ የሆነው አስር አለቃ መሳፍንት፣ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡

ከጦር ኃይሎች ሆስፒታል አገግሞ ከወጣ በኋላ፣ የት እንደተወሰደ ፌዴራል ፖሊስ ጭምር አለማወቁን ገልፆ ነበር፡፡

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በጄኔራል ሠዓረ መኮንን እና ጄኔራል ገዛኢ አበራ ግድያ ላይ ተሳትፏል በሚል በወቅቱ በጦር መሳሪያ ተመትቶ በመቁሰሉ በቁጥጥር ሥር የዋለው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ፣ ከጄኔራሉ የግል ጠባቂዎች አንዱ ነበር፡፡

ተጠርጣሪው ያለፉትን ወራት በከፍተኛ ሕክምና ላይ የቆየ ሲሆን፣ ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም በአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በዝግ ምስክርነት መስጠት መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት ከጦር ኃይሎች ሆስፒታል ህክምናውን ጨርሶ የወጣው አስር አለቃ መሳፍንት የሚሰጠው ምስክርነት ነገም እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com