የአማራ እና የቅማንንት ማኅበረሰብ ሥለ-ሠላም እየተወያየ ነው

Views: 190

የአማራ እና የቅማንት ማኅበረሰብ አባላት ሥለ-ሠላም የሚወያይ ጉባዔ በጋራ በማከናወን ላይ ናቸው፡፡

በጉባዔው ላይ ‹‹ከልዩነታችን ይልቅ፣ አንድነታችን ይልቃል፤ በእኛ ግጭት የሚያተርፉ የጸብ ነጋዴዎች ሊታቀቡ ይገባል፤ ከጀርባ ሆኖ በግጭት ማትረፍ አይቻልም›› ብለዋል፡፡

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም በጭልጋ ወረዳ ሰራባ ከተማ የሠላም ውይይቱ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ከሁለቱም የማኅበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እናቶችና ወጣቶች በውይይቱ ላይ ታድመዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ የሠላም ሚንስቴር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ውይይቱ፣ በሁለቱ ማኅበረሰቦች መካከል የነበረውን አብሮነት፣ አንድነትና ሰላማዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር እና ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚያስችል ቤተሰባዊ ምክክር  እነደሆነ ተነግሯል፡፡

ሁለቱ ማኅበረሰቦች ቤተሰባዊ ናቸው፤ በቤተሰብ መካከል የተፈጠረ ችግር ቤተሰብ ካልፈታው በቀር ማንም ሊፈታው አይችልም፤ በግጭቱም ማንም አሸናፊ ሊሆን አይችልም ያለፈው ላይመለስ ለዛሬና ለነገ ሰላማዊ ሂደት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com