የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ መጽሐፍ በፒዲኤፍ ተሰርቆ መውጣት እያነጋገረ ነው

Views: 214

በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተፃፈው ‹‹መደመር›› የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ከቀናት በፊት በኤሌክትሮኒክስ ቅጅ ወይም በፒዲኤፍ ተሰርቆ መውጣቱ ዜጎችን እያነጋገረ ነው፡፡

መጽሐፉ በኤልክትሮኒክስ ቅጂ ተሰርቆ መውጣቱ በሁሉም ሰው እጅ በቀላሉ እንዲገባ እና የተያዘለትን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ሂደት እንቅፋት ሊሆን እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ ዮናስ ዘውዴ ለአሐዱ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ድርጊቱ የመጽሐፉ ሽያጭ ላይ ያን ያክል ጉዳት ባያደርስም፣ መጽሐፉ በውስጡ ከያዘው ሃሳብ ባሻገር፣ በሽያጭ ገቢው ሊሰራ የታቀደውን ዓላማ ከዳር ከማድረስ አኳያ የሚወገዝ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጅ፣ የታቀደውን ዓላማ ከዳር ለማድረስ መጽሐፉ በፒዲኤፍ መውጣቱ የሚገዙትን ሰዎች እንደማያግዳቸው አማካሪው ገልፀዋል፡፡

ይህን መሰል ድርጊት የሚጠበቅ ነው ያሉት አቶ ዮናስ፣ ምንም እንኳን በገቢ መሰብሰብ ላይ ተፅዕኖ ቢኖረውም፤ መጽሐፉ በአጭር ጊዜ ለብዙ አንባቢዎች መድረሱም ትልቅ አዎንታዊ ጎን አለው ብለዋል፡፡

አማካሪው፣ መፅሐፉ የተያዘለት ዓላማ በሀገሪቱ የገጠር ክፍሎች የሚገኙ ታዳጊዎችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ለማድረግ በመሆኑ ዜጎች መጽሐፉን እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com