በአዲስ አበባ የመኪና-ዝርፊያ እና የመኪና-ቄራ አስጊ ሆኗል

Views: 365

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የመኪና-ዝርፊያ እና ‹‹የመኪና-ቄራ›› ተበራክቷል፡፡ በተለይ በግንባታ ሂደት ላይ በሚገኘው አዲሱ አደይ አበባ ስታዲየም አጥር ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የመኪና ስርቆት እና ‹‹እርድ›› እንደሚከናወን በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጸዋል፡፡

ከቦሌ መሠናዶ ትምህርት ቤት ከፍ ብሎ ካለው ‹‹ካልዲስ ካፌ›› አጠገብ ባለው አጥር ስር አሽከርካሪዎች መኪናቸውን አቁመው ሲወርዱ፣ በሩን የሚዘጉላቸው መስለው ክፍት በመተው አሽከርካሪው ከአካባቢው ሲርቅ ደግሞ መኪናውን በመክፈት ለዝርፊያ የሚያመቻቹ ወጣቶች መኖራቸውንና የመኪና በላቾችም ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ በመምጣት ግልጽ ዝርፊያ ፈጽመው ይሄዳሉ ብለዋል፡፡

በአካባቢው ዝርፊያው ሲፈፀም በምስል ቀርጸው ያያዙት ሰዎች ለኢትዮ-ኦንላይን ዘጋቢ እንደገለጹት፣ ‹‹ጉዳዩን ለፖሊስ ብናሳውቅም፣ እስከ አሁን መፍትሄ አላገኘንም›› ብለዋል፡፡

የአካባቢው ሰዎች ኹኔታውን ሲያብራሩ ‹‹ማንኛውም ሰው እዚህ አካባቢ መጥቶ ትንሽ ደቂቃ ቢቆይ፣ በመኪና ላይ የሚደረገውን ዝርፊያ በምስል መቅረጽ ይችላል፤ ፖሊሶችም ዘራፊዎችን እጅ ከፍንጅ መያዝ ይችላሉ›› ብለዋል፡፡

አሁን አሁን በአዲስ አበባ ከተማ እየተስፋፋ የመጣው ተሽከርካሪችን በመክፈት የሚካሄደው ዘረፋና ከፍ ሲልም እራሱን ተሽከርካሪውን ይዞ በመጥፋት ሙሉ አካሉን በመበታተን ለሽያጭ ማቅረብ (የመኪና ቄራ) የተለመደ ክስተት ከሆነ መሰነባበቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ የግል ተበዳዮችን ድምጽ እና ከከተማው ፖሊስ የምናገኘውን መረጃ ጨምረን በቅርቡ ሰፋ ባለ መልኩ አጠናቅረን በዩቲዩብ አድራሻችን እናቀርባለን፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com