“ብቸኛው መፍትሔ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ነው”

Views: 259

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት

የኢትዮጵያዊያን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሀን) ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ አሁን ላለንበት ሀገራዊ ችግር ብቸኛው መፍትሄ የሽሽግር መንግሥት ማቋቋም ብቻ ነው ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን ገለጹ፡፡

ለዚህ እንደ ምክንያት የጠቀሱት ደግሞ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ አይተን በማናውቀው  ኹኔታ ሰዎች በመንጋ ፍርድ እየተገደሉ ነው፤ ኢሕአዴግ እንደ ድርጅት እየተሰባበረ እና እየተዳከመ በመምጣቱ ዋነኛ ሥራው የሆነው የዜጎችን መብቶች ማስጠብቅ አልቻለም ብለዋል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ  ነገሮች ይሻሻላሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ የበለጠ እየተወሳሰበ መምጣቱ በኢሕአዴግ እና አጋር ድርጅቶች መካከል አለመግባባት በመከሰቱ ችግሮችን አባብሷል ሲሉ ሊቀመንበሩ ለኢትዮ-ኦንላይን ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ መከላከያ ኃይል እያለ፣ የደህንነት ተቋም እያለ፣ የገዢው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚው ኃላፊነቱን አለመወጣቱ እና ሀገር አደጋ ላይ መሆኑም የሽግግር መንግስት ማቋቋምን የግድ አድርጎታል ብለዋል፡፡

አሁን ሀገሪቱ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እየሄደች ነው ያሉት ኢ/ር ይልቃል፣ ይህ ነገር ከመከሰቱ በፊት አስቀድመን ተነጋግረን የአመለካከት ልዩነቶች ታርቀው ወደ ፊት የምንራመድበት የጋራ ራዕይ ፈጥረን የሽግግር ጊዜ ካበጀን በኋላ፣ ምርጫ እና ሌሎች ነገሮች መምጣት አለባቸው ብለዋል፡፡

ከሰሞኑም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕምድ እና በአክቲቪስት ጃዋር መሀመድ ደጋፊዎች በነበረው ሽኩቻ የ80 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ያስታወሱት ሊቀመንበሩ፣ እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች ቁጭ ብለው ተስማምተው ከተነጋገሩ እና የጋራ ሰነድ ካበጁ ከችግሩ መውጣት ይቻላል ብለዋል ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com