አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዲዔታ ሆነው ተሾሙ

Views: 197

የቀድሞው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት እና ክልሉን ለአንድ ዓመት የመሩት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ ሆነው መሾማቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሰባተኛው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መደበኛ ጉባዔ ላይ ደቡብ ክልልን እንዲመሩ የተመረጡት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ በጊዜው ደቡብ ክልልን ይመሩ የነበሩትን አቶ ደሴ ዳልኬን በመተካት ወደ ሥልጣን መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

አቶ ሚሊዮን ለአንድ ዓመት ክልሉን በማስተዳደር ቆይተው፣ በነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም ከአስተዳደር ሥልጣናቸው ተነስተው፣ በምትካቸው አቶ ርስቱ ይርዳው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡

(ዘገባው የአዲስ ማለዳ ነው)

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com