‹‹በአሰቦት ገዳም ላይ የተፈጠረ ነገር የለም›› ሲል የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ገለጸ

Views: 181

“በአሰቦት ገዳም በሚኖሩ መነኮሳት ላይ የተፈጠረ ነገር የለም” ሲል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ገለጸ፡፡

የአሰቦት የሴት መነኮሳት ገዳም በድንጋይ ሲደበደብ ማደሩን እና መነኮሳቱም  ለሚመለከተው አካል የአስቸኳይ የድረሱልን ድምጻቸውን ማሰማተቸውን በማሕበራዊ ትሥሥር ገጾች ላይ በስፋት ሲነበብ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ፣ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ እንጦስ፣ ‹‹ባለኝ መረጃ እና ሥራአስኪያጁ ሊቀሕሩያን ደረጄ እንዳደረሰኝ መረጃ ከሆነ፣ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም››  ሲሉ ለኢትዮ-ኦንላይን ገለጹ፡፡

‹‹የተባለው ነገር  ውሸት ነው፤ ከአሰበ ተፈሪ እኔ ጋር የመጡ አባቶችንም አናግሬያለሁ፤ እነርሱም ይህን ነው ያረጋገጡት›› ብለዋል- አቡነ እንጦስ፡፡

የሀገረስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ሕሩያን ደረጄ በበኩካቸው ለኢትዮ-ኦንላይን ሲገልጹ፣ በሴቶችም ይሁን በወንዶች ገዳም ተፈጠረ ስለተባለው ነገር ደውልን አጣርተናል፤ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ብለዋል፡፡

ሊቀሕሩያን ደረጄ አክለውም ‹‹ዛሬ ጠዋት ወደ ገዳሙ ደውዬ አጣርቻለሁ፤ ነገር ግን  ምንም የተፈጠረ ነገር የለም፤ የከፋ ችግር ሲያጋጥም  አባቶች ዝም አይሉም፤ ለሀገረስብከቱ ሪፖርት ያደርጋሉ፤ ሆኖም አሁን የደረሰን ሪፖርት የለም፡፡›› በማለት አስረድተዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com