በአማራ ክልል ከባሕር ዳር ወደ መርጦ ለማርያም ሲጓዝ የነበረ ተሸረርካሪ ተገልብጦ 17 ሰዎች ሞቱ

Views: 284

በአማራ ክልል፣ ከባሕር ዳር ወደ መርጦ ለማርያም መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ተገልብጦ፤ የአሥራ-ሰባት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ ሌሎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ትላንት ሐሙስ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከባሕር ዳር ወደ መርጦ ለማርያም ሲጓዝ የነበረው የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ግንብ አስተሪዮ አካባቢ በድንገት በመገልበጡ ነው የ17 ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ የቻለው ሲል የክልሉ ፖሊስ አሳውቋል፡፡

የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዛሬ እንደተናገሩት፣ ከሟቾች መካከል 12ቱ ወንዶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡

በተጨማሪም፣ ሰባት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል የደረሰባቸው ሲሆን፣ 12 ወንዶችና ስምንት ሴቶች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

ቀላል የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ደግሞ ሦስቱ ሕፃናት መሆናቸውንም ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በእለቱ፣ በመኪና መገልበጥ አደጋው የተጎዱ ዘጠኝ ተጓዦች ወደ ባሕር ዳር ለህክምና ተልከዋል ሲል አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

በክልሉ በመስከረም እና ጥቅምት ወራት ብቻ በደረሱ አምስት የትራፊክ አደጋዎች፣ የ77 ሰዎች ሕይወት ማለፉን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com