የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ-መስተዳድር ኢዜማ ፓርቲን ተቀላቀሉ

Views: 170

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ አኳይ ኦቻላ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲን በአባልነት መቀላቀላቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

አቶ ኦኬሎ፣ ቀደም ሲል ጋምቤላ ክልልን ለዘጠኝ ወራት በርዕሰ-መስተዳድርነት መምራታቸው ይታወሳል፡፡

ህወሓት/ ኢሕአዴግ በጋምቤላ የፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም፣ ከመጋቢት 1995 ዓ.ም ጀምሮም ሥልጣናቸውን ለቀው ከሀገር በመውጣት በሱዳን በስደት ላይ ሆነው የተቃውሞ ትግል ሲያደርጉም ቆይተዋል፡፡

ሆኖም፣ በ2007 ዓ.ም ህወሓት/ ኢሕአዴግ መንግሥት የደህንነት ሰዎች ከሱዳን አፍነው ወደ ሀገር ቤት ያመጣቸው ሲሆን፣ ለአራት አመታት ያህል በማዕከላዊ፣ ቃሊቲ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች ታስረው የነበረ ሲሆን፣ ከእስር ከተፈቱ በኋላም ወደ ኖርዌይ ተሰደዋል፡፡

ሰሞኑን ከኖርዌይ ተመልሰው በጋምቤላ የአኝዋክ ዞን ጎግ ወረዳ የኢዜማ ምርጫ መዋቅርን ተቀላቅለዋል ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com