ዜና

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

Views: 388

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ማይክ ፖፒዮ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መቶኛውን የኖቤል የሠላም ሽልማት በማግኘታቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት በውይይታቸው ላይ  አስተላልፈዋል ተብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አሜሪካ ታሪካዊውን የለውጥ ሂደት እንደምትደግፍ ጠቅሰው፣ በአሜሪካና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው ጠንካራ ወዳጅነት አስፈላጊኒት ማንሳታቸው ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ ዐቢይ እና ማይክ ፖምፒዮ በወቅታዊ ሀገራዊ ኹኔታ እንዲሁም ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መወያየታቸውን አስታውቋል፡፡

በደቡብ ሱዳን የሠላም ስምምነትና የጥምር መንግሥቱ ተግባራዊ እንዲሆን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማይክ ፖምፒዮ ጥሪ ማቅረባቸውም ተሰምቷል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com