ቦይንግ ኩባንያ ጥፋቱን በይፋ አመነ

Views: 193
  • እኔም ልቤ ተሰብሯል፤ በጥልቅ አዝናለሁ! የቦይንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ግዙፉ አውሮፕላን አምራች ድርጅት ‹‹ቦይንግ ኩባንያ›› 737 ማክስ ጀቶቹ ላይ የቴክኒክና የንድፍ ችግር እንደነበረባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ በይፋ አመነ፡፡

ትላንት በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የቀረቡት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ምዩለንበርግ፣ በ737 ማክስ ጀቶች ላይ ችግር እንደነበረባቸው እና የኩባንያው ጥፋት እንደሆነ አምነው “እኔም ልቤ ተሰብሯል፤ በጥልቅ አዝናለሁ” ብለዋል።

በተወካዮች ምክር ቤት የቦይንግ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት የትራንስፖርት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተጠይቀዋል።

በምክር ቤቱ የተጎጂዎች ቤተሰቦችና የሕግ ተወካዮቻቸውም ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የአሜሪካ ድምፅ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com