ለቺኩን ጉንያ በሽታ በቤት ውስጥ የሚረዱ ነገሮች

Views: 579

መግቢያ፡-

ከዚህ ቀደም በዚሁ ድረ ገጽ ላይ “መላ የወባ ትንኞች እንዳይናደፉ” በሚል ርዕስ ቺኩን ጉንያ (Chikungunya) ሻይረስ የሚያስተላልፉ ትንኞች፣ ከቤት እንዲርቁ ለማባረር ወይም በር አልፈው እንዳይገቡ ለመከላከል፣ እንዲሁም ቤት ቢገቡ እንኳን እንዳይናደፉ የሚረዱ ዘዴዎችን ገልፀን ነበር፡፡ ነገር ግን  የመከላከሉ ዘዴ ሳይሆን ቀርቶ በትንኞቹ ተነድፈው  በበሽታው የተያዙት  ቶሎ እንዲያገግሙ፣ በሽታውን እንዲቋቋሙ፣ የቫይረሱን የጉዳት ጫና ለመቀነስ ወይም በሽታውን ለመመከት እንዲያስችላቸው፤ ምን ቢመገቡ ይሻላቸዋል፣ ምን ቢጠጡ ጥሩ ይሆናል፣ ገላን እንዴት ይታጠቡ የሚለውን እና በቤት ውስጥ በቀላሉ የሚዘጋጁ ለቺኩን ጉንያ በሽታ ማስታገሻ የሚረዱ ነገሮች እናስተዋውቃለን፡፡

እነዚህም እንደ ዘቢብ፣ ጥሬ ካሮት፣ በሶቢላ፣ ዝንጅብል፣ እርድ፣ አስማ ዊድስ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ግራዋ፣ አብሽ፣ ፓፓያ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

 1. የቺኩን ጉንያ በሽታ ምልክቶች

በሽታውን በያዘች ትንኝ ከተነደፉ ከ 3 እስከ 7 ቀናት ውስጥ ምልክቶቹ ይጀምራሉ፡፡ ከምልክቶቹም፡-

 • ዋናው ትኩሳት እና የመገጣጠሚያ ህመም ሲሆኑ፤
 • ሌሎቹ
  • የራስ ምታት
  • የጡንቻ ህመም
  • የመገጣጠሚያ ዕብጠት
  • የሰውነት ላይ ሽፍታ (የቆዳ ማጉረብረብ)
  • አቅም ማነስ እና መዳከም ናቸው፡፡

ሁሉም የበሽታው ምልክቶች በአንድ ጊዜ አይከሰቱ ይሆናል፤ በሁሉም ሰው ላይ ተመሳሳይ ላይሆኑም ይችላሉ፡፡ እንደሰዉ እድሜ፣ በሽታን የመቋቋም አቅም እና ለበሽታው ማስታገሻ እንደሚደረገው ጥረት የበሽታው  ምልክቶች ወይም ጫና ሊለያይ ይችላል፡፡  ብዙ ጊዜ የቺኩን ጉንያ በሽታ ለሞት አያደርስም፡፡ ነገር ግን፣ የበሽታው ምልክቶች የሚያሰቃዩ እና አቅም የሚያሳጡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ብዙዎቹ በአንድ ሳምንት ይሻላቸው ይሆናል፡፡ ጥቂቶች ላይ የመገጣጠሚያ ህመም ለወራት ይዘልቃል፡፡ ለአደጋ ተጋላጭ የሚሆኑት በተለይም አዲስ የተወለዱ ጨቅላዎች፣ አረጋውያን እንዲሁም ከፍተኛ የደምግፊት፣ የስኳር እና የልብ ታማሚዎች ናቸው፡፡

አንዴ በበሽታው የተያዙት በአመዛኙ ወደፊት በዚህ በሽታ ብዙም አይጠቁም፡፡
ለበሽታው ምልክት የመረጃ ምንጭ https://www.cdc.gov/chikungunya/symptoms/index.html

 1. ዋናው የበሽታው ማገገሚያ ዘዴ
 • በቂ እረፍት ማድረግ
 • በቂ ውሃ መጠጣት
 • በህክምና የሚነገሩ ምክሮችን በአግባብ መከተል እና
 • በቤት ውስጥ እራስን ማከም ናቸው፡፡
 1. ለቺኩን ጉንያ (Chikungunya) በሽታ በቤት ውስጥ የሚረዱ ነገሮች

የመረጃ ምንጭ http://www.sanat.co.in/health-blog/62/chikungunya-herbal-remedies

             3.1    ለትኩሳት ማስታገሻ

             3.2   መገጣጠሚያ እና ለጡንቻ ህመም ወይም እብጠት ማስታገሻ

               3.3    ለሰውነት ቆዳ ማጉረብገብ ወይም ሽፍታ ማስታገሻ

              3.4 ለቺኩን ጉንያ ቫይረስ የመከላከል አቅም ለማጎልበትና የበሽታውን ጫና ለመቀነስ

በጠቅላላው ለቺኩን ጉንያ በሽታ የመከላከል አቅም ለማጎልበት፣ ተጓዳኝ የበሽታውን ጫና ለመቀነስ፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎችም ሆኑ፤ የበሽታው ስጋት ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እነዚህን ነገሮች ቢጠቀሙ በእጅጉ ይረዳቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፣

እዚህ ላይ የተገለፁት ብቻም ሳይሆኑ ሌሎችም የቺኩን ጉንያን ቫይረስ፣ የደንጉ ቫይረስ እና የወባ  በሽታ ጫና የሚቀንሱ ብዙ የተፈጥሮ ተክሎች አሉ፡፡ ይበልጥ አንብቡ፡፡ ያነበባችሁትን ለሌሎች ንገሩ፡፡ የታመሙትን እግዚአብሔር ይማራቸው፡፡    መልካም ንብባ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com