ዜና

የመገናኛ ብዙኃን ም/ቤት የመተዳደሪያ እና የሥነ ምግባር ደንብ ሊፈረም ነው

Views: 325

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ም/ቤት፣ የም/ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ (Memorandum of Understanding) እና የሥነ ምግባር ደንብ (Code of Conduct) የም/ቤቱ አባላት ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አደረገ፡፡

ም/ቤቱ ይህንኑ አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ማህበሩ ሕጋዊ እውቅና ማግኘቱን መሠረት በማድረግ ጠቅላላ ጉባዔው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት በነገው ዕለት ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ የአንድ ቀን ስብሰባ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ም/ቤት፣ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ሕጋዊ ምዝገባ አግኝቶ ከ30 በላይ የመገናኛ ብዙኃንን እንዲጎለብት የበኩሉን ገንቢ አስተዋጽኦ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com