የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከፈተ

Views: 174

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት በብሩንዲ የነበረውን የአፍሪካ አኅጉር ጽሕፈት ቤቱን በወቅቱ በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት አንስቶ በጆኔቭ ካዘዋወረ ከብዙ ዓመታት በኋላ አሁን በኢትዮጵያ ሊከፍት ችሏል፡፡

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ጽሕፈት ቤቱን ወደ አፍሪካ ለማስመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ ኬንያ እና ሌሎች ስምንት የአፍሪካ አገራት በእጩነት ቀርበው ነበር ያሉት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለሚከፈተው ጽሕፈት ቤት ከስምንቱ እጩዎች መካከል ተመራጭ የሆነችው ከሌሎቹ እጩዎች በንፅፅር ሲታይ አንፃራዊ ሠላምና ፀጥታ ያላት ከመሆኗም በላይ የአፍሪካ ሕብረት እና የልዩ ልዩ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የተለያዩ የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ ነው፡፡

ይህ ተቋም በአፍሪካ አገራት ያሉትን የሜትሮሎጂ ሃይድሮጂን አቀናጅቶ የመምራት ዕድል የሚሰጥ እና በአኅጉሪቱ የዓየር ጠባይ መለዋወጥ እያጠና የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ጽሕፈት ቤቱ ከጥቅምት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በከፈተው ቢሮው ሥራውን መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com