በደቡብ ጉባዔ የኃላፊዎች ሹም-ሽር እና ሥንብት ይጠበቃል

Views: 309

ጉባዔው በ2ተኛ ቀኑ በኮንታ ልዩ ወረዳ በአደጋ ሕይወታቸው ያጡ 17 ዜጎችን በህሊና ጸሎት አስቧል

በመጪው ዓርብ በሚጠናቀቀው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ ላይ፣ የኃላፊዎች ሹም-ሽር እና የዳኞች ሥንብት ሊኖር እንደሚችል ምንጮች ለኢትዮ-ኦንላይን ገለጹ፡፡ ጉባዔው በዛሬው ውሎው በኮንታ ልዩ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎችን በህሊና ጸሎት አስቧል፡፡

በጉባዔው ላይ የሚገኙ የመሥተዳድሩ የዜና ምንጮች እንደገለጹት፣ በአሁኑ ጊዜ ክልሉ በአንፃራዊ ሠላም ውስጥ ቢገኝም፣ በክልሉ መንግሥት ሥር ሆነው፣ ከክልሉ እና ከፌዴራል መንግሥት አቅጣጫ ውጪ የሚሰሩ አካላት እና ቡድኖች አሉ፡፡

የክልሉ መሥተዳድር፣ የክልሉንና የፌዴራል መንግሥት አቅጣጫን ትተው፣ በተቃራኒው የሌሎች የፖለቲካ ኃይሎችን ፍላጎት በርቀት ሊያሳኩ የሚሞክሩ ኃይሎችን የማጥራት ሥራ ለማከናወን ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

በዚህ ምክንያትም በጉባዔው ማጠናቀቂያ የባለሥልጣናት፣ የኃላፊዎች እና የዳኞች ሹም-ሽር ይከናወናል ሲሉ ምንጮች አሳውቀዋል፡፡

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈጉባዔ ወ/ት ሄለን ደበበ እንደገለጹ ት፣ የሕብረተሰቡን ባህሪ እና ለውጡን በቅጡ ያልተረዱ ኃይሎች በክልሉ አለመረጋጋት ቢፈጥሩም፣ በአሁኑ ጊዜ አንጻራዊ ሠላም ሰፍኗል ሲሉ በትላንትናው የጉባዔው መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡

ጉባዔው በአራት ቀናት ውስጥ በዘጠኝ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ መርሃ ግብር የተያዘለት ሲሆን፤ በዛሬው እለት ሁለተኛን አጀንዳ ማገባደዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com