ዜና

ግጭት በሚፈጥሩ የቅማት ኮሚቴ አባላት ላይ ርምጃ እንደሚወስድ የአማራ ክልል የሰላም ግንባታና ደህንነት ቢሮ አስታወቀ

Views: 441

የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ደህንነት ቢሮ ሓላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር ለኢትዮ ኦን ላይን እንደገለፀት ከህወሓት የገንዘብ እና የሥልጠና ድጋፍ እየተደረገላቸው ግጭት በሚፈጥሩ የቅማት ኮሚቴ አባላት ላይ ርምጃ ለመውሰድ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።

“የቅማንት የማንነት ጥያቄ በክልሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በሕገ መንግሥቱ ምላሽ አግኝቷል። አሁን ያለው ኮሚቴ አሸባሪ ነው። የማንነት ጥያቄ ሳይሆን የያዘው የውክልና ጦርነት ነው። የማንነት ጥያቄ የያዘ መስሎት በስህተት የሚከተለው አካል ካለ እውነቱን ሊያውቅ ይገባል። ከደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ቀጥሎ የማንነት ጥያቄ በአግባቡ የተመለሰው አማራ ክልል ውስጥ ነው። ” ብለዋል አቶ አገኘሁ በተለይ ከኢትዮ ኦን ላይን ጋር በነበራቸው ቆይታ።

የማንነት ጥያቄው እንደተነሳ በመጀመሪያ 42 ቀበሌዎችን ያካተተ የቅማንት አስተዳደር እንዲመሰረት የአማራ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወስኗል። ቀጥሎም ያልተካተቱ ቀበሌዎች እንዳሉ በመጠቀሱ አስተዳደሩ 69 ቀበሌዎችን እንዲይዝ ተደርጓል።

በሕገ መንግሥቱ መሰረት አንድ ብሔር በራሱ አስተዳደር የሚመራው ተመሳሳይ ማንነት፣ተመሳሳይ ቋንቋ ካለው እና በአንድ መልክዓ ምድር ውስጥ የሚኖር ከሆነ ነው።

እንደ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለፃ አሁን ወደ ቅማንት አስተዳደር እንዲካተቱ ጥያቄ የቀረበባቸው ሦስት ቀበሌዎች ግን ከስልሳ ዘጠኙ የቅማንት ቀበሌዎች ርቀው በመተማ የሚገኙ ናቸው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com