ዜና

ጠ/ሚ ዐብይ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

Views: 201

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ ዘጠኝ መቶ ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ሽልማት ይቀበላሉ

የአየር ለውጥ መብት ተሟጋች የሆነችው ስዊድናዊቷ የ16 ዓመት ታዳጊ ግሬታ ተንበርግ ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል እድል ተሰጥቷት ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትረሩ 100ኛው የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ ይሆዋል።

የኖቤል ሽልማት በየዓመቱ በፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ሕክምና፣ ሥነጽሑፍና ሰላምዘርፎች ይሰጣል።

ሽልማቱ የሚሰጠው ባለፉት 12 ወራት “ለሰው ልጅ የበለጠ አበርክቶ” የሚያደርጉ ነገሮችን ላከናወኑ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ሲሆን ኖቤል የሚለው ስያሜ የተወሰደው ከሲውዲናዊ ነጋዴ እና የድማሚት ፈጣሪ አልፍሬድ ኖቤል መሆኗም ይታወቃል::

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com