ዜና

ኢትዮጵያዊው ጦማሪ ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ

Views: 225

ዓለም አቀፉ ‹‹ፔን ፒንተርስ›› የሽልማት ሥነ-ስርዓት፣ ኢትዮጵያዊውን የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ሕብረት መስራች አባል ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉን ሸለመ፤ ‹‹ዓለም አቀፍ ጀግና›› ሲልም ሰይሞታል፡፡

የሀሮልድ ፒንተር ማስታወሻ የሆነው ይህ የሽልማት ሥነ-ስርዓት በእንግሊዝ ብሔራዊ ቤተ-መጽሐፍት ትላንት ምሽት ተካሂዷል፡፡

የ2019 ዓ.ም የፔን ፒንተርስ ሽልማትን ያገኘው ጋዜጠኛና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ‹‹የመፃፍ ነፃነት ወይም የመናገር ነፃነት በለውጥ እና በአመጽ መካከል ያለ መንገድ ነው›› ብሏል፡፡

‹‹ጦርነትም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ፣ ዓለምን ለመቀየር እንደ ጽሑፍ ያለ ኃይል የላቸውም፤ የሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ ሳንጥል፣ በሰላማዊ መንገድ ሀሳባችንን በጽሑፍ ማቅረብ እንችላለን›› ሲል በሽልማት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ለዚህ ሽልማት የበቃው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ሕብረት ላይ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቃወም የሚያስችል መድረክ በመፍጠሩ ነው፡፡

ሕብረቱ አራት ዋና ዋና የድህረ ገጽ ዘመቻዎችን በመክፈት የኢትዮጵያ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር ጥሪ በማድረግ ቅስቀሳ ማካሄዱ ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ከዚህ ቀደም ጦማሪ በመሆኑና በነበረው ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ ተሳትፎ ብቻ ለአራት ጊዜያት ያክል ተወንግሎ ለእስር ተዳርጓል፡፡

ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሽልማቶችን እንደተበረከቱለት ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com