ዜና

በአዲስ አበባ ጥቅምት ሁለት የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ አስተባባሪው ባልደራስ ነገ በፅህፈት ቤቱ መግለጫ ይሰጣል

Views: 209

 በጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ሰብሳቢነት የሚመራው የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት(ባልደራስ) ነገ ለፊታችን እሁድ ጥቅምት ሁለት ቀን 2012 ዓ.ም ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ ምክር ቤቱ ሰልፉን አስመልክቶም ነገ አርብ መስከረም 30 ቀን ከረፋዱ አራት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ጀምሮ አዲስ አበባ አራዳ ጊርጊስ አቅራቢያ በሚገኘው ፅህፈት ቤቱ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ሲከበር ክልላዊ መንግሥታቸው አዲስ አበባን እንደተቆጣጠራት ተናግረዋል፡፡ ይህም የአዲስ አበባን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚገረስስ እንደሆነ ነዋሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለፁ ነው፡፡ በመሆኑም በሰላማዊ ሰልፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን ቅሬታቸውን እንደሚገልፁ ይጠበቃል፡፡

ፈረንሳይ ለጋሲዮ፣ሳሪስ፣አውቶብስ ተራ እና ጎፋን ጨምሮ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ነዋሪዎች ለተቃውሞ ሰልፉ እየተዘጋጁ መሆኑንም በተዘዋወርንባቸው አጋጣሚዎች ተመልክተናል፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት እንቅስቃሴ ቢያደርጉም መንግሥትና የሰልፉ አስተባሪዎች ባደረጉት ድርድር ተከልክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ከዚህ በፊት ያቀዳቸው የውይይትና የጋዜጣዊ መግለጫ ፕሮግራሞች በተደጋጋሚ በመንግሥት መከልከላቸው ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com