ዜና

አሥራ ሁለተኛው የሰንደቃላማ ቀን በመጭው ሰኞ ይከበራል

Views: 359

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰንደቃላማ ቀን በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የተቀመጠውን ትርጓሜ መሰረት በማድረግ የወጣ የሰንደቃላማ አዋጅ ቁርር 654/2001 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሳምት ሰኞ እንዲከበር ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረት የፊታችን ሰኞ ጥቅምት ሦስት ቀን እንደሚከበር የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡ ሰንደቃላማው መሀል ላይ በተቀመጠው አርማ ብሔራዊ አለመግባባት መኖሩንም ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግገጫ አስታውቋል፡፡

ባለፈው አመት አስራ አንድኛው የሰንደቃላማ ቀን በተለያዩ ልዩነቶችና ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተከብሯል፡፡ በሰንደቃላማው ላይ ያሉ ተቃውሞዎች አሁንም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ሕዝባዊ ውይይቶች ተደርገው ብሔራዊ ሰንደቃላማው እንደሚቀየር መንግሥት ባለፈው አመት ቃል ቢገባም እስካሁን በሰንደቃላማ ጉዳይ ሕዝባዊ ውይይት አልተደረገም፡፡ ሰንደቃላማውም አልተቀየረም፡፡

በተመሳሳይ ሕገ መንግስቱም ሰፊ ቅሬታዎች እየተነሱበት ነው፡፡ እንዲሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲቀየር የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጠይቀዋል፡፡ መንግሥት በቅርቡ ሶማሊኛ፣ትግረኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋዎች ከአማርኛ በተጨማሪ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ጥናት መጀመሩ አስታውቋል፡፡ በጥናቱ መሰረት ተጨማሪ የፌዴራል የሥራ ቋንቋዎች የሚኖሩ ከሆነ ሕገ መንግሥቱ ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ይጠበቃል፡፡ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔው መሰረት አዎንታዊ ምላሽ የሚያገኝ ከሆነ ሕገ መንግሥቱ እንዲሻሻል ይጠበቃል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com