ዜና

የኢትዮጵያ የህፃናት የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል አዲስ የሞባይል ስልክ መተግበሪያ አስተዋወቀ

Views: 604

የልብ ህሙማን ህፃናትን ለመርዳት የኢትዮጵያ የህፃናት የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር “ለልቤ ይሁን” በሚል ስያሜ ይፋ ያደረጉት አዲስ መተግበሪያ ነው፡፡

የህፃናት የልብ ህክምና ሃኪም ዶክተር ሺቢቆም ታምራት  የህክምና አገልግሎቱን ሽፋን ለማሳደግና የልብ ማእከሉን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የስልክ መተግበሪያው ተግባራዊ እንደተደረገ ገልጸዋል፡፡

በማእከሉ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት በአሁኑ ጊዜ ከስምንት ሺህ በላይ ህሙማን ወረፋ እየተጠባበቁ ቢሆንም ማእከሉ ባለበት የኢኮኖሚ ውስንነት በአመት አምስት መቶ ህሙማንን ብቻ እያከመ ይገኛል።

ዶክተር ሺቢቆም እንዳታወቁት ከሆነም  “ለልቤ ይሁን” የሚለውን የስልክ አገልግሎት በነፃ በመጠቀም ህብረተሰቡ የልብ ማእከሉን ማገዝ ይቻላል፡፡

ቴክኖሎጂውን የመንግስትና የእምነት እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች እንዲጠቀሙት ለማድረግ የታሰበ ሲሆን የልብ ህክምና ማእከሉ አቅም ከተጠናከረ ወደፊት በአመት ለአንድ ሺህ 500 ህሙማን ህክምናውን ማዳረስ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

አዲሱ መተግበሪያ በሚቀጥለው ሳምንት በይፋ አገልግሎቱን እንደሚጀምርም የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ቀደም በማእከሉ ህክምናውን ያገኙ ቤተሰቦችም ህብረተሰቡ አፕሊኬሽኑን  እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com