ዜና

ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለ493 የመንግስት ሰራተኞች ሽልማት አበረከቱ

Views: 309

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅር ታከለ ኡማ በከተማ አስተዳደሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ለሚያገለግሉ እና በስራቸው ጥሩ አፈጻጸም ላስመዘገቡ 493 ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት አበረከቱ፡፡

የማበረታቻ ሽልማቱ የውጪ ሀገር ትምህርትና ስልጠናን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶች የተካተተበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በሽልማቱ ከፅዳት ሰራተኞች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለሙያዎች ድረስ እንደተካተቱበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሽልማቱን ያበረከቱት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ እንዳሉት በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም ሆኑ ተቋማቱ ህብረተሰቡን በትክክለኛ መንገድ ማገልገል ዋነኛ አላማቸው አድርገው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም እነዚህ የመንግስት ሰራተኞች ህዝብን በአግባቡ በማገልገል ባሳዩት መልካም ስራ ሽልማቱ እንደተበረከተላቸው ተናግረዋል፡፡

የመንግስት ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሲወጡ የሀገር አንድነትና የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ የሚለወጥበት ዕድል ይፈጠራል፤ የዚህ ዕድል ውጤትም ለትውልድ የሚተርፍ ይሆናል ብለዋል፡፡

ሽልማቱ የተበረከተላቸው ሰራተኞች በተቋማቱ አመራሮች የተሻለ አፈጻጸም አላቸው ተብለው የተመረጡ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

የሽልማቱ ስነ-ስርዓት የተከናወነው ትላንት መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ቢሮ አስታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com