ዜና

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎቹ ላይ የ86 ከመቶ ክፍያ ጨመረ

Views: 432

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ላይ የሰማኒያ ስድስት ከመቶ ጭማሪ አደረገ፡፡ በክፍያው መጨመር ምክንያት የምዝገባ ጊዜው መስከረም 11 ቢያልፍም፣ እስካሁን በግል ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል አንዳቸውም አለመመዝገባቸውን ኢትዮ ኦን ላይን ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ አባላት ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

ሆኖም፣ ከክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃውን አልገለፁልን፤ ለመመረቂያ ጽሑፍ ለመመዝገብ እያንዳንዱ የግል (extesion) ተማሪ 18 ሺህ ብር እንዲከፍል ተጠይቋል።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ለንግድ ሥራ ትምህርት ቤት ዲን በጽሑፍ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፕሬዝዳንቱ በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት የተወሰነ በመሆኑ፣ ውሳኔው አይቀየርም ማለታቸውን ተማሪዎች ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሀና በተደጋጋሚ ብለንደውልም የስልክ ጥሪው አልተመለሰም።

ተማሪዎቹ ተመዝግበው ትምህርት የጀመሩት በ2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማለትም ከቦርዱ ውሳኔ 1 ዓመት በፊት ነው። በመሆኑም በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተወሰነ ውሳኔ ይመለከታችኋል መባሉ ሕገ-ወጥ መሆኑን በሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com