በዘይት ጀሪካን ወደ መሐል አገር ሊገባ የነበረ ከ50 ሺህ በላይ ጥይት ተያዘ

Views: 392

ከየመን በጅቡቲ አድርጎ ወደ መሐል አገር በዘይት ጀሪካን ውስጥ ተሸሽጎ ሊገባ የነበረ ለተለያዩ መሳሪያዎች የሚያገለግል ከ50 ሺህ በላይ ጥይት፤ 20 ክላሺንኮቭ መሳሪያና አንድ ሽጉጥ በዐፋር ክልል ተያዘ፡፡

መሳሪያው የተያዘው ትላንት መስከረም 13 ቀን 2012 ዓ.ም በአፋር ክልል ኤሌደአር ወረዳ ዲችኦቶ ቀበሌ በተለያዩ አካባቢዎች ሌላ ዕቃ በማስመሰል ጥይቶቹን በዘይት ጀሪካን በማድረግ ወደ መሐል አገር ለማስገባት ሲሞከር በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፤ በክልሉ ፖሊስና በሕብረተሰቡ ክትትል ሊያዝ ችሏል ተብሏል፡፡

በክልሉ ባሳለፍነው ሳምንትም በተመሳሳይ መልኩ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እንዲያልፍላቸው የፖሊስ መኮንኑን በገንዘብ አታለው ወደ መሐል አገር መሳሪያዎችን ለማስገባት ሲሞክሩ ወጣቱ የፖሊስ መኮንን ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ድለላቸውን ባለመቀበል በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መካላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አህመድ ሁመድ ተናግረዋል፡፡

ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በኮሚሽኑ ሥም ላበረከቱት አርዓያነት ያለው ፖሊሳዊ ተግባር ሽልማት አበርክቶለታል፤ ቀደም ሲል ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለዋና ሳጅን ሲራጅ፣ ምሥጋና እና የምስክር ወረቀት አበርክተውላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com