ዜና

መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን ዋጋ ለማስላት አማካሪ እየፈለገ ነው ተባለ

Views: 393

የገንዘብ ሚንስቴር፣ የኢትዮ-ቴሌኮም-ን አጠቃላይ ሃብት በማወቅ ዋጋውን ከማስላት ባሻገር፤ ከባለቤትነት ድርሻውና ከሥራው ምን ያክሉ ለግል ኩባንያዎች ይሸጥ የሚለውን ለመወሰን፣ አማካሪ ተቋም በመፈለግ ላይ መሆኑን አሳወቀ፡፡

ባለፈው ሐምሌ ወር የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት የውጭ ኩባንያዎች በአገሪቱ የቴሌኮም ገበያ እንዲሰማሩ ፈቃድ ለመስጠት መዘጋጀቱንም ይታወሳል፡፡

አሁን በከፊል ለግል ኩባንያ ይሸጣል የተባለው ኢትዮ-ቴሌኮም፣ በአፍሪካ በዘርፉ ከተቋቋሙ ቀደምት ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑም ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከኢትዮ ቴሌኮም ባሻገር የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ድርሻዎች በከፊል ለግል ኩባንያዎች ለመሸጥ ያሳለፈው ውሳኔ አሁንም አወዛጋቢ ሆኗል፡፡

የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ ቢያደንቁም፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን አገሪቱ ልትከተል በመረጠችው መንገድ አልተስማሙም፡፡

ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ  ኢትዮ ቴሌኮም ለዓመታት በብቸንነት ተቆጣጥሮት ወደ ነበረው ገበያ ተወዳዳሪ ከመግባቱ በፊት፣ አራተኛው ትውልድ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት መስጠት ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከስድስት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ የአራተኛውን ትውልድ (4G) በመላው ኢትዮጵያ ደግሞ (3G) አገልግሎት ለማስፋፋት የ700 ሚሊዮን ዶላር ውል ከቻይናው ሑዋዌ ኩባንያ ጋር ተፈራርሞ ነበር።

በአፍሪካ እና በዓለም የቴሌኮም ገበያ የከበረ ስም ያላቸው በርካታ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ገበያ ኢትዮ ቴሌኮምን ለመገዳደር ፍላጎታቸውን አሳይተዋል፡፡

ዘገባው የሮይተርስ ነው

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com