የተመ ለጦማርያን እና ጋዜጠኞች ሥልጠና ሰጠ

Views: 298

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዮኔስኮ)፣ በመጪው መስከረም 17 ቀን 2012 ዓም (28 Sep, 2019 እኤአ) በዓለማቀፍ ደረጃ የሚከበረውን ዓለማቀፍ መረጃ የማግኘት መብት በማስመልከት፣ ለአፍሪቃ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ሥልጠና ሰጠ፣ ኢትዮጵያዊያን ጦማርያንና ጋዜጠኞች ተጋብዘዋል።

በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስካይላይት ሆቴል ዛሬ ጠዋት በጀመረው ሥልጠና ላይ፣ ሃሳብን በነፃነት የማራመድ ሰብዓዊና ዓለማቀፍ መብት፣ ለመረጃ ተደራሽ የመሆን እድል፣ የዲጂታል ሚዲያ ባህርይን (ICT) በቅጡ መረዳት፣ የመረጃና የመገናኛቴክኖሎጂ ባለድርሻ አካላትን ጠንቅቆ ማወቅ፣ በተግባቦት ሙያ ለተሰማሩ ባለሟሎች በሀሰት ዘገባ ተሰስተው ከማሳሳት ሊታደጋቸው እንደሚችል በሥልጠናው ላይ ተወስቷል።

በሌላም በኩል፣ ዜጎች የትክክለኛ መረጃ ተደራሽ እንዳይሆኑ ከሚያሰናክሉ የተግባቦት እክሎች ባለሟሎች ሊጠነቀቁ እንደሚገባ ተገልጿል።

መረጃን አጣርቶ በፍጥነት ከማቅረብ ባሻገር እጅግ ግነት (ኩሸት)ን፣ የሀሰት ዘገባን እና የሆነ አካል ለተለየ ፍላጎቱ ሊያራምደው ከሚፈልገው የሀሰት ዜና፣ ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስል በቅጡ ተረድቶ መቆጣጠር፣ በዋናነት የባለሟሉ ተግባር መሆን አለበት ተብሏል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com