ዜና

ቻይና ድህነት ቅናሳ ላይ የሚሰራ የበጎ-ሥራ ተቋም በኢትዮጵያ ከፈተች

Views: 203

ቻይና በኢትዮጵያ ድህነት ቅነሳ ላይ ሊያግዝ የሚችል የበጎ-ሥራ ተቋም (ፋውንዴሽን) በአዲስ አበባ ከፈተች፡፡

የChina Foundation for Poverty Alleviation ወይም በምህጻረ ቃል (CFPA) የተባለ ድርጅት በአዲሰ አበባ በትላንትናው ዕለት በይፋ ተከፍቷል፡፡

የቻይና አምባሳደር ታና ጂያን፣ ፋውንደሽኑ ከቻይና ኢንትርፕራይዞች እና ግብረ- ሠናይ ድርጅቶች በጋራ በመሆን ይሰራል ብለዋል፡፡

እዲሁም፣ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከለል በማኅበራዊ ኃላፊነት እና በወዳጅነት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም፣ ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በንግድ እና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ግንኙነታችንንም ያጠናክርልና ሲሉ ተናግረዋል፡

በአጠቃላይ፣ የበጎ-ሥራ ተቋሙ፣ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞች፣ የንጹህ ውኃ ፕሮጀክት፣ የት/ቤት የውኃ ማጣሪያ ፕሮጀክት እና ሴቶች በኢኮኖሚ ብቁ እንዲሆኑ ለመደገፍ ይሰራል ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com