ዜና

በትግራይ ክልል የ15 ዓመቷን ታዳጊ ሊድሩ የነበሩ ቤተሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

Views: 189

ሀደሩ ገብራይ የተባቸውን የ15 ዓመቷን ታዳጊ ያለ እድሜዋ ጋብቻ እንድትፈፅም በትግራይ ቆላ ተምቤን አካባቢ ሽር-ጉድ ሲሉ የነበሩ ቤተሰቦቿ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

ታዳጊ-ወጣት ሀደሩ በሕይወቷ አንዴም አግኝታ የማታውቀውንና በእድሜ እጅግ የሚበልጣትን የወደፊት ባሏን እድታገባ ሽር-ጉዱ የተከናወነው የታዳጊዋ ባል ይሆናል በተባለው ግለሰብ እና በቤተሰቦቿ አማካይነት እንደነበርም ታዳጊዋ ተናግራለች፡፡

ሆኖም፣ ሠርጉ ይከናወናል የተባለበት መርሃ-ግብር  በፖሊስ አማካይነት እንዲቀር ተደርጎ፣ ባል ይሆናል የተባለው ግለሰብ እና ቤተሰቦቿ መታሰራቸው ታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ ከጥቂት ጊዜ እሥራት በኋላ፣ ቤተሰቦቿ ሠርጉ እዲቀር በመስማማተቸው በዋስ እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡ እርሷም ለደህንነቷ ሲባል በሚል ከቤተሰቦቿ ጋር የእሥር ተጋሪ ሆና ነበር፡፡

ታዳጊ-ወጣት ሀደሩ፣ ‹‹ሠርጉ ሲሰረዝ ትንሽ ቅር ተሰኝቼ ነበር፤ ምክንያቱም ቤተሰቦቼ ለሠርጉ ብዙ ልፋትና ወጪ አውጥተዋል፤ ሆኖም ግን፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ደግሞ ከትምህርቴ ጋር የሚሄድ አይደለም ብላለች፡፡

የትግራይ የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዓለማት አማረም፣ ይህን ጎጂ ባሕላዊ ድርጊት ለመከላከል ከጤና፣ ትምህርት፣ ከሕግ አስፈፃሚዎች እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴርም ከኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛትን እንደ አውሮፓወያኑ የጊዜ ቀመር እስከ 2024 ዓ.ም ለማስቆም ቃል በመግባት ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱም ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ከአምስት ሴቶች አንዷ፣ ከ18 ዓመት በታች ባለው ዕድሜ ጋብቻ ትፈጽማለች መባሉንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com