ዜና

የ10.7 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ ያሸነፈው ሚካኤል ገብሩ በአዲስ አበባ ተገደለ

Views: 302

በካናዳ የ10.7 ሚሊዮን ዶላር የሎተሪ ዕጣ ያሸነፈው ትውልደ-ኢትዮጵያዊው አቶ ሚካኤል ገብሩ፣ በአዲስ አበባ ከተማ በዘራፊዎች ተገድሎ መገኘቱ ታወቀ፡፡

ሟቹ በቋሚነት በካናዳ አገር የሚኖር ትውልደ-ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ በካናዳ ቶሮንቶ በሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት ታስቦ ውሏል፡፡

ግድያው የተፈፀመው በተደራጁ ዘራፊዎች እንደሆነም ሲ ጂ ቲ ኤን፣ የካናዳ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን (ሲቢሲ)ን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ብዙኃን መገናኛ ዘግበዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃኑ ጉዳዩን የኢትዮጵያ መንግሥት ብዙኃን መገናኛ አለመዘገባቸውን አስታውሰዋል፡፡

ሆኖም፣ በኢትዮጵያ ራዲዮ ኤፍ ኤም 97 ላይ በአወያይ-ጋዜጠኝነት የሚታወቀው እና በካናዳ ኑሮውን መሠረተው ዳግማዊ ታሪኩ፣ ከሟቹ ቤተሰቦች ጉዳዩን መስማቱን ጠቅሶ በማኅበራዊ ገፁ ማስፈሩን ጠቁመዋል፡፡

ግድያው በማን እና እንዴት እንደተፈፀም ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የፖሊስ አካላት ወንጀሉን ለማጣራት እንቅስቃሴ ስለ መጀመር አለመጀመራቸውም በዘገባው ላይ አልተገለፀም፡፡

እንዲህ ዓይነት የተደራጁ የቡድን ዘራፊዎች የተጠና ጥቃትና ዘረፋ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ተባብሶ መቀጠሉን ዘገባው አውስቷል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com