ዜና

“የትግራይ ሕዝብ ‹በወረዳ ደረጃ እንደራጅ› ብሎ የጠየቀው ዴሞክራሲያዊ መብቱን ነው”

Views: 187
  • ህወሓት መልስ መስጠት ያለፈለገው እንደ ሽንፈት ቆጥሮት ነው

የትግራይ ህዝብ ‹‹በወረዳ ደረጃ እንደራጅ›› ብሎ የጠየቀው ጥያቄ፣ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ነው ሲል ዓረና ለፍትሕና ለዴሞክራሲ (ዓረና) ፓርቲ አስታወቀ፡፡ ሙሉ ለሙሉ በህወሓት የሚመራው የክልሉ መንግሥት በበኩሉ፣ ሳይንሳዊ ጥናት በማካሄድ የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ በሂደት ላይ ነኝ ማለቱ ይታወሳል፡፡

በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለዓመታት ሲነሱ የቆዩ ‹በወረዳ ደረጃ እንደራጅ› የሚሉ የሕዝብ ጥያቄዎች፣ ተገቢውን ምላሽ ሳያገኙ እንደቀሩ የዓረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዶም ገ/ሥላሴ ለኢትዮ-ኦንላይን አስታውቀዋል፡፡

ዓረና ፓርቲ  የትግራይ ሕዝብ የጠየቀው የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው ህውሓት ግን ምላሽ መስጠት ያልፈለገው ሽንፈት ስለመሰለው ነው ብሏል፡፡

ሕብረተሰቡ በወረዳ ደረጃ የመደራጀት ጥያቄ ያነሳውም የተለያዩ አገልግሎቶችን በአካባቢያቸው ለማግኘት በማሰብ ነበር የጠየቁት ሲሉ የዓረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዶም ገ/ሥላሴ ለኢትዮ-ኦንላይን አስታውቀዋል፡፡

አቶ አንዶም እንደተናገሩት፣ ሕብረተሰቡ የአስተዳደር አግልግሎት ለማግኘት ብሎ እስከ 300 መቶ ኪሎ ሜትር በመሄድ እየተቸገረ ስለሆነ፣ የክልሉ መንግሥት አጥጋቢ ምላሽ መስጠት አልቻልም ብለዋል፡፡

ይህም የሆነበት ምክንያት ህወሓት ለህዝብ ጥያቄ ምልሽ መስጠትን እንደ ሽንፈት ስለሚቆጥረው  ነው ብሏል፡፡

ኅብረተሰቡ ይህን ጥያቄ ያነሳው ለአካባቢው በጀት ጉዳይ ነው ብሎ የሚያጥላላው ህወሓት ራሱ  ለተሃድሶ እና ለተለያዩ ወጪዎች የህዝብ ገንዘብን ሲያወጣና ሲያባክን እንያለን፤ ይህም፣ ምክንያታዊም አይደለም ብለን እንደ ዓረና ፓርቲ እናምናለን ብለዋል፡፡

የወረዳ ጥያቄ ያቀረቡት ብዙዎች እንደሆኑ የተናገሩት አቶ አንዶም፣ ከህወሓት በፊት  አብዛኛዎቹ ወረዳዎች የነበሩ ናቸው፤ አሁንም ወደ ወረዳ ደረጃ እንመለስ የሚልም ጥያቄ ነው ያቀረቡት ብለዋል፡፡

ተምቤን ኣካባቢ ያሉ ሰዎችም አስተዳደራዊ ግልጋሎት ለማግኘት ወደ አክሱም ለማቅናት ብዙ ኪሎ ሜትሮችን እየተጓዝን እንግልት ላይ ስለሆንን፣ ዞን እንሁን የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ዞን  የሚባል ነገር በትግራይ ክልል ይቀራል እየተባለ ነው ሲሉ አቶ አንዶም ለኢትዮ-ኦንላይን ገልጸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com