ዜና

የኢትዮጵያ- ዱባይ ዲያስፖራ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

Views: 189

ለሁለት ቀናት የሚቆየው የኢትዮጵያ – ዱዳይ ዳያስፖራ ቢዝነስ ፎረም በትላንናው ዕለት በሸራተን አዲስ ተከፈተ፡፡

የቢዝነስ ፎረሙ በኢትዮጵያ እና በተባበሩት ዐረብ ኤሜሬቶች በሚገኙ የንግድ ማኅበረሰብ መካከል ግንኙነታቸውን ለማጠንከር እና የንግድ ሥራዎቻቸውን ለማስተዋቅ ዕድል ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በፎረሙ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ከሆነም ፎረሙ ለኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት  ለመሳብም ይረዳል ብለዋል፡፡

በአሁን ወቅት ኢንቨስተሮች ብዙ ችግሮችን እየተጋፈጡ መሆኑን የተናገሩት አምባሳደሩ፤ ኢንቨስትምንቱን ለመሳብ እየተሰራ እንደሆን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በተባበሩት ዐረብ ኤሜሬቶች መካከል የሰዎች ለሰዎች ግንኙነት እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደርሰው እየሰሩ መሆናቸውንም አስታውሰዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com