ዜና

አርመኒያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ልትከፍት ነው

Views: 191

የአርመን ሪፐብሊክ መንግሥት ኤምባሲውን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዱን የሀገሪቱ ብዙኃን መገናኛ የሆነው አርመን ፕሬስ ዘግቧል፡፡

አርመኒያ  ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ዲፕሎማሲያዎ ግንኙነቷን ለማጠናከር የሚረዳት አማራጭ እንዲሁም አምባሳደሮች  እንደሌላትም ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የሚከፈተው ኤምባሲ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መጠናከር ብቻ ሳይሆን በአፍሪቃ ለሚኖራት ግንኙነት ጉልህ ድርሻ  ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በኤምበሲ አመሰራረት ጉዳይ ላይም በነገው ዕለት በእስራኤል ምክክር እንደሚደረግበት ተሰምቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ እና አርመኒያ ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በንግድ፣ በሀይማኖት እና በሌሎች ጉዳዮች የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላቸው ይታወሳል፡፡

የአርመን ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ወስጥ ይኖሩ የነበረ ሲሆን፣ በሃይማኖት ረገድም የራሳቸው የአርመናውያን ‹‹ፖስቶሊክ›› ቤተክርስትያን አላቸው፡፡

እንዲሁም የሁለቱ አገራት ግንኙነት በይበልጥ የተጠናከረው ደግሞ በመጀመረያ የዓለም ጦርነት ወቅት በቱርክ እና በአርመኒያ መካከል በተደረገው ጦርነት አርመናዊያን ሀገር የለሽ ዜጎች ሆነው በዓለም ላይ ሲበተኑ ነበር፡፡

ቱርክ በአርመናዊያን ላይ በፈጸመቸው የዘር ጭፍጨፋ ምክንያት አገራት አርመናዊያንን እያስጠለለ ሲያኖር፣ ኢትዮጵያም አርመናዊያን ህጻናት ወይም ‹‹አርባ ልጆች›› በመባል የሚታወቁት ህፃናት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አባታዊ ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት እንዲኖሩ አድርጋለች፡፡

ንጉሱም ይህን የወሰኑት በኢየሩሳሌም የምትገኘውን የአርመኒያ ገዳምን  በጎበኙበት ወቅት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ዕድገት የአርመን ተወላጆች ድርሻ ከፍተኛ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በ40 ልጆች ቁጥር ልክ የሙዚቃ መሳሪያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡

‹‹አርባ ልጆች›› አዲሰ አበባ የገቡት በ1924 ሲሆን፣ ከባንዱ መሪ ከኮቮርክ ላንባንዲያን ጋር መምጣታቸውም ይነገራል፡፡

በዚህም ሳቢያ፣ የንጉሰ ነገስቱ የመጀመሪያው ኦርኬስትራ ባንድ በማቋቋም የንጉሠ ነገሥቱ  ዘብ በመሆን ከ1930 እስከ 1974 አገልግሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com