ኢትዮጵያ ከቡና ገበያ 183 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

Views: 197

ኢትዮጵያ በሁለት ወር ውስጥ ወደ ውጭ አገራት ከላከቸው የቡና ምርት፣ ከ183 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እዳገኘች ተገለጸ፡፡

52 ሺህ ሦስት መቶ ቶን ቡና ወደ ውጭ አገራት የተላከ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር የ6 ሺህ 585 ቶን ብልጫ አለው ተብሏል፡፡

በገቢ ደረጃም የ6 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ማሳየቱን እና ከእቅድ በላይ ማከናወኑንም የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን በብዛት በመግዛት ቀዳሚ አገራት ጀርመን፣ ሳውዲ ዐረቢያ እና ጃፓን ሲሆኑ፤ አሜሪካ፣ ቤልጄም፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ሱዳን እና አውስትራሊያም ኢትዮጵያ የቡና ምርቷን ከምትልክባቸው አገራት ውስጥ ይገኙበታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com