ባለአደራ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው

Views: 158
  • ኦዴፓ፣ የታከለ ኡማ አስተዳደር እና ቀሲስ በላይ ተናበው እየሰሩ ነው ብሏል

ማክሰኞ ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በወቅታዊ ሀገራዊ ኹኔታ ላይ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ አገር ብዙኃን መገናኛ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ‹‹ሶር አምባ ሆቴል›› ፊት-ለፊት በሚገኘው ጽ/ቤቱ መግለጫ ለመስጠት መሰናዳቱን አስታወቀ፡፡

ባለ አደራ ምክር ቤቱ፣ ለኢትዮ-ኦንላይን በላከው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው፣ ዓርብ መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 በአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ዋና ጽ/ቤት በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሀገራዊ ኹኔታን በዝርዝር ይዳስሳል፤ ከብዙኃን መገናኛ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል ተብሏል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱን በበላይነት እየመራ የሚገኘው የኦሮሞ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኦዴፓ)፣ በም/ል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ መሥተዳደር እና ራሱን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሊነጥል እየሰራ የሚገኘው የእነ ቀሲስ በላይ መኮንን የ‹‹ኦሮሚያ ቤተክህነት ጽ/ቤት›› በድብቅ ግንኙነት ተናበው እየሰሩ ነው ሲል ለኢትዮ-ኦንላይን አመላክቷል፡፡

ስለዚህ፣ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመስቀል አደባባይና በተለያዩ ከተሞች የሚደረገውን ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በተመለከተ፤ የ‹‹ኦሮሚያ ቤተ ክህነት አዳራጅ ኮሚቴ›› ሰብሳቢ ስለተባሉት ቀሲስ በላይ መኮንን ስለ አዲስ አበባ ከተማ የተናገሩትን በማስመልከት እና በኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢና አዲስ አበባን በሚመራው ኦህዴድ መካከል ስላለው የድብቅ ግንኙነት ጋዜጣዊ መግለጫው ያተኩራል ብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com