እነ ቀሲስ በላይ ይቅርታ አንጠይቅም አሉ

Views: 158

ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን 2011 ዓ.ም እነ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ ‹‹የኦሮሚያ ቤተክህነት ጽህፈት ቤት›› እንዲቋቋም ባደረግነው እንቅስቃሴ ብጹሀን አባቶች ሊያስገድዱን ቢሞክሩም፣ ያጠፋነው ነገር ስለሌለ ይቅርታ መጠየቅ አይገባንም ሲሉ ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

እነ ቀሲስ በላይ፣ ያለ ሲኖዶስ ፈቃድ የ‹‹ኦሮሚያ ቤተክህነት ጽ/ቤት››ን እንመሰርታለን ብለው መንቀሳቀሳቸውና ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ጥፋት ስለሆነ ይቅርታ እንዲጠይቁ ብጹሀን አባቶች መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

ይቅርታ መጠየቅ አስፈላጊ ከሆነ መጠየቅ ያለባቸው ብፁሃን አባቶች ናቸው ምክንያቱም ላለፉት ዓመታት የቤተክርስቲኗን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ የፖሊቲካና የኢኮኖሚ ፍላጎታቸውን ሲሟሉባት ስለነበሩ ህዝብን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ እንፈልጋለን ሲሉ እነ ቀሲስ በላይ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው መግለጫቸውም ላይ ይቅርታ የማይጠይቁበትን ምክንያት ሲገልጹ፣ የተፈለገው የቤተክርስቲያኗን ቀናኢ ልጆችን ብሶትና ፍላጎት ለመግለፅ፤ ላለፉት ረጅም ዓመታት በተለይም ለኦሮሞ ህዝብ ተደራሽ ያልሆነ መዋቅርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ ነው፡፡

እንዲሁም፣ ሲኖዶሱ መግለጫ እንዳይሰጥ ክልክሏል ብለን ስለማናስብ እና ህዝቡም መግለጫውን በከፍተኛ ተነሳሽነት እየጠበቀ ስለነበር ነው ብሏል፡፡

‹‹ጥያቄያችንን ቅዱስ ሲኖዶስ ባይቀበለውም፣ የምስረታ ሂደታችንን አናቆምም›› ሲሉ ከዚህ በፊት ለኢትዮ ኦንላይን መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com