ዜና

ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ- ትምህርት ጉባዔ ባለሟሎችን አነጋገረ

Views: 201

ሀገር አቀፍ ‹‹የአጠቃላይ ትምህርት›› ሥርዓተ-ትምህርት ጉባዔ፣ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት በሚዘልቀው የሀገሪቱ ሥርዓተ-ትምህርት (ካሪኩለም) አተገባበር ላይ አገር በቀል ያልሆነ አቅጣጫ መያዝ ባለሟሎችን አነጋገረ፡፡ ለትምህርት ጥራት፣ ሥርዓተ-ትምህርቱ ከፖለቲካና ከሃይማኖት ይውጣ፤ አመራሩም ሙያተኛ ብቻ ይሁን ተብሏል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት (ረቡዕ እና ሃሙስ) በስካይ ላይት ሆቴል በተከናወነው ጉባዔ ላይ የሟዕለ-ህፃናት እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የስትራቴጂና የአተገባበር ፍኖተ ካርታ በውጭ አገራት ባለሟሎች ንድፍ መሄዱ አግባብ አይደለም ሲሉ ተችተዋል፡፡

ሀገር አቀፍ ‹‹የአጠቃላይ ትምህርት›› ሥርዓተ-ትምህርት ጥናትና ጉባዔውን ለማከናወን የቴክኒክ ድጋፍ ያደረጉት ‹‹ኬምብሪጅ አሰስመንት ኢንተርናሽናል ኤዲኴሽን›› የተባለ ድርጅት እና ‹‹ዩኒሲኤፍ›› ናቸው፡፡

ዋናውን ጥናት ያከናወነው ‹‹ኬምብሪጅ አሰስመንት›› ነው ያሉን የትምህርት ሚንስቴር የዜና ምንጮች፣ ጥናቱ የተከናወነው በአጠቃላይ ሥርዓተ ትምህርት ካሪኩለም ላይ ነው፤ የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት ምን መምሰል አለበት፣ የሥርዓተ ትምህርቱ ሠነዶች ይናበባሉ ወይ፣ ጥራት ያለው ሥርዓተ ትምህርት ለመቅረጽ ምን ያስፈልጋል፣ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራውስ ምን ይመስላል የሚል ሲሆን መፍትሄውም ከውጪ የሚመጣ (አዶብት የሚደረግ) ሆኗል፤ ሀገር አቀፍ የአብነት እና የመድረሳ ትምህርት ተሞክሮ ቦታ አልተሰጠውም፤ ብለዋል፡፡

‹‹መዋዕለ ህፃናትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሉ ልጆች ራሳቸውን፣ የአካባቢያቸውን ባህልና ማንነታቸውን እንዲያውቁ በእናት ቋንቋቸው ይማሩ በምንልበት በዚህ ጊዜ፣ የሀገር ውስጥ የካሪኩለም ባለሙያ ሳይጠፋ፣ የውጪ ባለሙያዎች መጥተው ቋንቋችንን፣ ባህላችንን፣ ሥነ-ልቦናችንን፣ የወል ባህሪይ እና እምነታችንን ሳይረዱ ካሪኩለም እንዲቀርጹልን መፍቀድ ሀገራዊና የትውልድ ክስረት ነው የሚያመጣው ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com