የመስከረም አራቱ ሰልፍ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ እንደሚጠብቅ ተነገረ

Views: 163

መስከረም አራት ሊካሄድ በታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ለመጠበቅ አስተባባሪዎቹ መስማማታቸው ተነገረ፡፡

በመጪው መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉትን ችግሮች በተመለከተ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎቹ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ለመጠበቅ መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡

ትላንት ነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጽህፈት ቤት 15 የመንፈሳዊ ማህበራት የተውጣጡ ተወካዮች በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቱ እያጋጠሟት ካሉ ችግሮችና አሁን የኦሮሚያ ቤተክህነትን ነጥለው የማቋቋም ጉዳይን አንስተው ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባውም በመጪው መስከረም ወር በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፉን ዛሬ አድርጉም አታድርጉም ብዬ አልፈቅድምም፤ አልከለክልምም፤ ምክንያቱም ሲኖዶሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስብሰባ ላይ ስላሉ ለቀረቡት ጥያቄዎች መፍትሔ ይገኛል ብዬ አስባለሁ ብለዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባውን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ሰልፉ ስለመካሄድና አለመካሄዱ ጥቅም መልስ ስለሚሰጥ ለጊዜው የሲኖዶሱን ውሳኔ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ምክትል ከንቲባው ያቀረቡትን ሀሳብ የመንፈሳዊ ማህበራት የተውጣጡ ተወካዮችም ተስማምተውበታል ተብሏል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com