አርቲስት ተዘራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

Views: 172

አርቲስት ተዘራ ለማ ትላንት ምሽት በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

በ1954 ዓ.ም በፍቼ ከተማ ተወለዶ በመዲናችን አዲስ አበባ ሪቼ አካባቢ ነው ያደገው፤ አርቲስቱ የሶስት ሴት ልጆችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር፡፡

አርቲስቱ ቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ጌም እየተጫወት ድንገት ከተቀመጠበት ሸርተት ብሎ በመውደቁ ቤተሰቦቹና የአካባቢው ሰው ተረባርቦ ወደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጣቢያ ሲወስዱ ትንፋሹ እንደነበረች ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ሰዎች አርቲስቱን ወደ ጤና ጣቢያ አድርሰውት ከወጡ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈች መስማታችን ይናገራሉ፡፡

አርቲስት ተዘራ ወደ ጥበቡ ከገባበት ጊዜ በፊልም፤ በቴሌቪዥን ድራማ፤ በትያትርና ልዩ ልዩ ማስታወቂያዎች ላይ ሰርቷል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com