ልዩ ኃይሉ የተቃውሞ ሰልፎችን ለመበተን የጎማ ጥይት መጠቀም መጀመሩን ተናገረ

Views: 174

የሶማሌ ክልል፣ ሌሎች አገራት የተቃውሞ ሰልፎችን ጉዳት ሳያስከትሉ ለመበተን የሚጠቀሙበትን  የጎማ ጥይት መጠቀም መጀመሩን የክልሉ ልዩ ኃይል ፖሊስ ጄኔራል መሐመድ አሕመድ መሐሙድ ተናገሩ፡፡

ከዚህ በፊት በሀገራችን የተለያዩ አድማዎችንና የተቃውሞ ሰልፎችን ለመበተን የሰውን ህይወት የሚያጠፋ ጥይት ነበር የሚተኮሰው፡፡

ይህ የጎማ ጥይት ግን ሰዎችን ከመታ በኋላ ግፋ ቢል የማቁሰል እንጂ የመግደል አቅም የለውም ተብሏል፤ ከአሁን በኋላ በሶማሌ ክልል ማነኛውም ፖሊስ ተቃውሞዎችን ለመበተን አንድም ገዳይ ጥይት አይተኩስም ተብሏል፡፡

በቅርቡ ጥቅም ላይ የዋለውን የተቃውሞ መበተኛ የጎማ ጥይትን መጠቀም መጀመራቸው ሰልፈኞቹን ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስባቸው ወይም ጥይትን ሳይጠቀሙ እንዲበተኑ የሚያርግ ነው ሲሉ ጄኔራሉ ተናግረዋል፡፡

ጄኔራሉ እንደገለፁት፣ ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 27 ቀን 2011 በሶማሌ ክልል ሸበሌ ወረዳ ከባድ መሳሪያዎችን ይዘው ለአመፅ የወጡ ሰልፈኞችን የክልሉ ልዩ ኃይል በሰላማዊ መንገድ መበተን መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ሰልፈኞቹ መንግሥት የጎሳ ግጭቶችን ለማስቀረት ብሎ አዲስ መንደሮችን እየፈጠረ ሰዎችን ማስፈር በመጀመሩ ብዙዎች ጉዳዩን ተቃውመው በመውጣታቸው  ምክንያት በተፈጠረው ኹከት አስር ፖሊሶች ቆስለዋል ብሏል፡፡

አዲሱ ጄኔራል መሐመድ ለቢቢሲ ሶማሊኛ ክፍል እንደተናገሩት፣ የክልሉ ልዩ ኃይል በከፍተኛ የለውጥ ሂደት ውስጥ ነው ያለው ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com